ዘፀአት 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቍርበት፥ ሰማያዊ ቀለም የገባ ቍርበት፥ የማይነቅዝ ዕንጨት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቈዳ፣ የለፋ ቈዳ፣ የግራር ዕንጨት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተለፍቶ ቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፤ የተለፋ የፍየል ቆዳ፥ የግራር እንጨት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍየልም ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራርም እንጨት፥ |
“ከማይነቅዝ ዕንጨት መወርወሪያዎችን ሥራ፤ በድንኳኑ በአንደኛው ገጽ ላሉ ሳንቆች አምስት መወርወሪያዎችን፥
ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎች ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም የናስ እግሮች አድርግላቸው።
ሰማያዊም፥ ሐምራዊም፥ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለ በፍታም፥ የፍየል ጠጕርም፥ ቀይ የአውራ በግ ቍርበትም፥ የአቆስጣ ቍርበትም ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።
ከማይነቅዝ እንጨትም ታቦቱን ሠራሁ፤ እንደ ፊተኞችም ሁለት የድንጋይ ጽላት ቀረፅሁ፤ ወደ ተራራውም ወጣሁ፤ ሁለቱም ጽላት በእጄ ነበሩ፤