ወደ አውድማ ዳርም በደረሱ ጊዜ ላሞቹ ሰረገላውን ሲስቡ የእግዚአብሔር ታቦት ዘንበል ብላለችና ታቦቷን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።
ዘፀአት 19:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይደፋፈሩ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ውረድና አሮንን ከአንተ ጋራ ይዘኸው ውጣ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት መጣደፍ የለባቸውም፤ አለዚያ እርሱ ቍጣውን ያወርድባቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም፦ “ሂድ፥ ውረድ፤ አሮንንም ከአንተ ጋር ይዘህ ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እንዳያጠፋቸው ወደ ጌታ ለመውጣት አይተላለፉ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ውረድና አሮንን ይዘህ ና፤ ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ወደ እኔ ለመውጣት ወሰኑን ማለፍ የለባቸውም፤ ይህን ቢያደርጉ ግን እኔ እግዚአብሔር እቀጣቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ውረድ፤ አንተ አሮንም ከአንተ ጋር ትወጣላችሁ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን እግዚአብሔር እንዳያጠፋቸው ወደ እግዚአብሔር ይወጡ ዘንድ አይተላለፉ አለው። |
ወደ አውድማ ዳርም በደረሱ ጊዜ ላሞቹ ሰረገላውን ሲስቡ የእግዚአብሔር ታቦት ዘንበል ብላለችና ታቦቷን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።
ለሕዝቡም በዙሪያው ወሰን አድርግላቸው፤ ወደ ተራራው እንዳትወጡ፥ ከእርሱ ማንኛውንም ክፍል እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል” ብለህ ንገራቸው፤
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮንም፥ ናዳብም፥ አብዩድም፥ ከእስራኤልም ሰባ ሽማግሌዎች ወደ እግዚአብሔር ውጡ፤ በሩቁም ለእግዚአብሔር ስገዱ፤
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
“ኦሪትም ነቢያትም ከጥንት ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ ይጋፋል።
ታዲያ ኦሪት ለምን ተሠራች? ኦሪትስ ኀጢአትን ታበዛት ዘንድ፥ ተስፋ ያደረገለት ያ ዘር እስኪመጣ ድረስ፥ በመላእክት በኩል በመካከለኛው እጅ ወረደች።
ነገር ግን ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ይሆን ዘንድ፥ ያመኑትም ያገኙት ዘንድ፥ መጽሐፍ ሁሉን በኀጢአት ዘግቶታል።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።