ዘፀአት 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በዚች ቀን በሚያዝያ ወር ወጥታችኋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በዚች ዕለት በአቢብ ወር ወጥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ቀን፥ የዓመቱ መጀመሪያ በሆነው በአቢብ ወር ግብጽን ለቃችሁ ወጥታችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ዛሬ በአቢብ ወር ወጥታችኋል። |
የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።