ዘፀአት 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና በእጅህ እንደ ምልክት ፥ ከዐይኖችህም እንደማይርቅ ነገር ይሁንልህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ እኛን ከግብጽ ያወጣን ስለ ሆነ ይህ ሥርዐት በእጅህም ሆነ በግንባርህ ላይ እንደ ምልክት ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶናልና በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዓይኖችህም መካከል እንደ ተንጠለጠለ ነገር ይሁንልህ።’” |
ደሙም ባላችሁባቸው ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም አያለሁ፤ እናንተንም እሰውራችኋለሁ፤ እኔም የግብፅን ሀገር በመታሁ ጊዜ የጥፋት መቅሠፍት አይመጣባችሁም።
እንዲህም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምንድን ነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ እንዲህ ትለዋለህ፦ እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር አወጣን፤
እግዚአብሔርም በበረታች እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና የእግዚአብሔር ሕግ በአፍህ ይሆን ዘንድ በእጅህ እንደ ምልክት፥ በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋልና፥ በተዘረጋችም ክንድ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።”
ስለዚህም ፈጥነህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከግብፃውያንም ተገዥነት አወጣችኋለሁ፤ ከባርነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ፤ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፤
የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጣቸው፤ ወገኖቹንም በተሰደዱበት በምድረ ግብፅ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ከዚያም ከፍ ባለ ክንዱ አወጣቸው።
“እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፤ በዐይኖቻችሁም መካከል እንደማይንቀሳቀስ ይሁኑ።
እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ዕለተ ሰንበትን ትጠብቃትና ትቀድሳት ዘንድ አዘዘህ።
አንተ ልጅህን በለው፦ በግብፅ የፈርዖን ባሪያዎች ነበርን፤ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ፥ በተዘረጋችም ክንድ ከዚያ አወጣን፤
ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ ሌሎችንም በዙሪያቸው ያሉ የአሕዛብን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡት።