የፋሲካውንም በግ እንደ ሙሴ ሥርዐት በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸትና በሰታቴ፥ በድስትም ቀቀሉ፤ ተከናወነላቸውም፤ ለሕዝቡም ልጆች ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
ዘፀአት 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእሳትም የተጠበሰውን ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣውን እንጀራም ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋውንም በዚያችው ሌሊት በእሳት ላይ ጠብሰው ከመራራ ቅጠልና ከቂጣ ጋራ ይብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ በእሳት የተጠበሰውን ካልቦካ ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውንም በዚያኑ ሌሊት እየጠበሱ ከመራር ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር ይብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል። |
የፋሲካውንም በግ እንደ ሙሴ ሥርዐት በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቍርባን በምንቸትና በሰታቴ፥ በድስትም ቀቀሉ፤ ተከናወነላቸውም፤ ለሕዝቡም ልጆች ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፤ በአውራጃዎቻችሁ ሁሉ እርሾ አይኑር።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
ሕጉን በውጭ አነበባችሁ፤ የታመነም አላችሁት፤ በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ትጠብሰዋለህ፤ ታበስለዋለህም፤ ትበላውማለህ፤ በነጋውም ተመልሰህ ወደ ቤትህ ትሄዳለህ።