Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 34:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “እርሾ ካለው ከማንኛውም ነገር ጋራ የደም መሥዋዕት ለእኔ አታቅርብ፤ ከፋሲካ በዓል የተረፈው መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይቈይ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ካለው ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የፋሲካው በዓል መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይደር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ለእኔ የእንስሶች መሥዋዕት በምትሠዉበት ጊዜ ደሙን እርሾ ካለበት ኅብስት ጋር አታቅርቡልኝ ለፋሲካ በዓል ከታረደው እንስሳ ምንም ሥጋ እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ አታቈዩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የፋሲካውም በዓል መሥዋዕት እስከ ነገ አይደር። የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ታገባለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 34:25
12 Referencias Cruzadas  

ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት አን​ዳች አታ​ስ​ቀሩ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም ከእ​ርሱ አት​ስ​በሩ፤ ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት የተ​ረፈ ቢኖር በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት።


እርሾ ያለ​በ​ትን ምንም አት​ብሉ፤ በቤ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ውስጥ ቂጣ ብሉ።”


በእ​ሳ​ትም የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ሥጋ​ውን በዚ​ያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣ​ውን እን​ጀ​ራም ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የበ​ዓ​ሌም ስብ እስ​ኪ​ነጋ አይ​ደር።


ከቅ​ድ​ስ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ወይም እን​ጀራ እስከ ነገ ቢተ​ርፍ፥ የቀ​ረ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ ነውና አይ​በ​ላም።


“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ታ​ቀ​ር​ቡት የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ እርሾ አይ​ሁ​ን​በት፤ እርሾ ያለ​በት ነገር፥ ማርም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ይሆን ዘንድ አታ​ቀ​ር​ቡ​ምና።


“ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነው የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋም ለእ​ርሱ ነው፤ በሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቀን ይበ​ሉ​ታል፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አያ​ተ​ር​ፉም።


ከእ​ር​ሱም እስከ ነገ ምንም አያ​ስ​ቀሩ፤ ከእ​ር​ሱም አጥ​ን​ትን አይ​ስ​በሩ፤ እንደ ፋሲካ ሥር​ዐት ሁሉ ያድ​ር​ጉት።


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


የቦ​ካ​ውን እን​ጀራ ከእ​ርሱ ጋር አት​ብላ፤ ከግ​ብፅ ሀገር በች​ኮላ ስለ ወጣህ ከግ​ብፅ ሀገር የወ​ጣ​ህ​በ​ትን ቀን በዕ​ድ​ሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ፥ ቂጣ እን​ጀራ ሰባት ቀን ከእ​ርሱ ጋር ብላ።


ሰባት ቀንም በሀ​ገ​ርህ ሁሉ የቦካ አይ​ታ​ይም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማታ ከሠ​ዋ​ኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይ​ደር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos