Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 34:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 “የመሥዋዕቴን ደም እርሾ ካለው ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የፋሲካው በዓል መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይደር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “እርሾ ካለው ከማንኛውም ነገር ጋራ የደም መሥዋዕት ለእኔ አታቅርብ፤ ከፋሲካ በዓል የተረፈው መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይቈይ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ለእኔ የእንስሶች መሥዋዕት በምትሠዉበት ጊዜ ደሙን እርሾ ካለበት ኅብስት ጋር አታቅርቡልኝ ለፋሲካ በዓል ከታረደው እንስሳ ምንም ሥጋ እስከ ማግስቱ ጠዋት ድረስ አታቈዩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቴን ደም ከቦካ እን​ጀራ ጋር አት​ሠዋ፤ የፋ​ሲ​ካ​ውም በዓል መሥ​ዋ​ዕት እስከ ነገ አይ​ደር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ እንጀራ ጋር አትሠዋ፤ የፋሲካውም በዓል መሥዋዕት እስከ ነገ አይደር። የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ታገባለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 34:25
12 Referencias Cruzadas  

የመሥዋዕቴን ደም ከቦካ ቂጣ ጋር አትሠዋ፤ የበዓሌም ስብ እስከ ንጋት ድረስ አይቆይ።


ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋት የቀረውንም በእሳት አቃጥሉት።


የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።


ከእርሱም እስከ ማግስቱ ጥዋት ድረስ ምንም አያስቀሩ፥ ከእርሱም አጥንትን አይስበሩ፤ እንደ ፋሲካ ሥርዓት ሁሉ ያክብሩት።


“ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ሥጋ በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አያሳድር።


ከተቀደሰው ሥጋ ወይም ቂጣ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ስለሆነ አይበላም።


እርሾ ያለበትን ምንም አትብሉ፥ በምትኖሩበትም ቦታ ሁሉ ያልቦካ ቂጣ ብሉ።”


ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ በእሳት የተጠበሰውን ካልቦካ ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት።


ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማያት አንዲት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


“ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን።


በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios