እኔ አገልጋይህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ፤ ጌታዬንም ንጉሡን ልቀበል ወረድሁ።”
ዘፀአት 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፥ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት፥ በእናንተም ላይ በደልሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር በእናንተም ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠራና እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ አምላካችሁንና እናንተን በደልሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አምላካችሁን እግዚአብሔርንና እናንተን በድያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፤ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ። |
እኔ አገልጋይህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ፤ ጌታዬንም ንጉሡን ልቀበል ወረድሁ።”
ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኀጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድያለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ተናገረው።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ጓጕንቸሮቹን ከእኔ፥ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
በለዓምም የእግዚአብሔርን መልአክ፥ “በድያለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆምህብኝ አላወቅሁም፤ እንግዲህ አሁን አትወድድ እንደሆነ እመለሳለሁ” አለው።
ሳኦልም ሳሙኤልን፥ “ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ አሁንም በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊትና በእስራኤል ፊት እባክህ አክብረኝ፤ ለአምላክህም ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ” አለው።
ሳኦልም፥ “በድያለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመለስ፤ ዛሬ ነፍሴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከዚህ በኋላ ክፉ አላደርግብህም፤ እነሆ፥ ስንፍና እንደ አደረግሁና፥ እጅግ ብዙም እንደ ሳትሁ ዐወቅሁ” አለ።