ዘፀአት 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዙ፤ እጅግም ጸኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለአዋላጆቹ መልካም ሆነላቸው፤ ሕዝቡም በቍጥር እየበዛና እያየለ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ለአዋላጆቹ መልካም ነገርን አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፥ እጅግም ብርቱ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ እግዚአብሔርም ለእነርሱ መልካም ነገር አደረገላቸው፤ ለያንዳንዳቸውም ቤተሰብ ሰጣቸው፤ በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ በቊጥር እየበዙና ብርቱዎችም እየሆኑ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፤ እጅግም በረታ። |
ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፤ እጅግም ጸኑ ፤ ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች ይጸየፉአቸው ነበር።
የበደለ ከጥንት ጀምሮ ከዚያም በፊት ኀጢአትን አድርጓል፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁና፤
ክፉ ምክርን መክረዋልና ለነፍሳቸው ወዮላት! እንዲህም አሉ፥ “ጻድቁን እንሻረው፤ ሸክም ሆኖብናልና፤” ስለዚህ የእጃቸውን ሥራ ፍሬ ይበላሉ።
እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስለ አገለገላችሁ፥ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችትሁን ሥራ፥ በስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።