መክብብ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠቢብ ድሃ ሰውም በውስጥዋ ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፤ ያን ድሃ ሰው ግን ማንም አላሰበውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፥ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያች ከተማ የሚኖር ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ከተማይቱን በጥበቡ አዳናት፤ ይሁን እንጂ ያንን ድኻ ማንም አላስታወሰውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፥ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም። |
ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከተማው ሕዝብ ሁሉ በብልሀት ነገረቻቸው፤ የቢኮሪን ልጅ የሳቡሄን ራስ ቈርጠው ሰጡአት፤ ወደ ኢዮአብም ጣለችው። ኢዮአብም መለከቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከተማዪቱ ርቆ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ ሄደ። ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
ለብልህ ከአላዋቂ ጋር ለዘለዓለም መታሰቢያ የለውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመጣልና ሁሉም ይረሳል፤ ብልህስ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል?
እንዲሁም ያንጊዜ ኃጥኣን ወደ ጽኑ መቃብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅድስት ስፍራም ወጥተው ተለዩ፤ እነርሱም በከተማዋ ተመሰገኑ፥ እንዲህ ሠርተዋልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።