መክብብ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብን አውቅ ዘንድ በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀንና በሌሊት እንቅልፍን በዐይኑ የሚያይ የለምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብን ለማወቅና ሌት ተቀን እንቅልፍ የማያውቀውን በምድር ያለውን የሰውን ድካም ለመገንዘብ በአእምሮዬ ስመረምር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብን አውቅ ዘንድ፥ በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን በሰጠሁ ጊዜ፥ በቀንና በሌሊት እንቅልፍን በዓይኑ የማያይ አለና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበበኛ ለመሆንና በዚህ ዓለም የሚደረገውንም ነገር ሁሉ መርምሬ ለማወቅ በሞከርኩ መጠን ሰው ሌት ከቀን ዕረፍት አጥቶ እንደሚኖር ተረዳሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥበብን አውቅ ዘንድ በምድር የሚሆነውንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀንና በሌሊት እንቅልፍን በዓይኑ የማያይ አለና፥ |
ከሰማይም በታች ስለተደረገው ሁሉ በጥበብ ለመመርመርና ለመፈተን ልቤን አተጋሁ፤ እግዚአብሔር ይደክሙበት ዘንድ ክፉ ድካምን ለሰው ልጆች ሰጥትዋልና።
አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ? ሰውነቴንስ ከደስታ ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።
አውቅና እመረምር ዘንድ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ መደምደሚያ እፈልግ ዘንድ፥ የክፉዎችንም ስንፍናና ዕብደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።
ይህን ሁሉ በአንድነት አየሁ፥ ከፀሓይም በታች ወደ ተደረገው ሥራ ሁሉ ልቤን ሰጠሁ፤ ሰውም ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ።