La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የጠ​ቢ​ባን ልብ በል​ቅሶ ቤት ነው፤ የሰ​ነ​ፎች ልብ ግን በደ​ስታ ቤት ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የአላዋቂዎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሁልጊዜ ስለ አስደሳች ነገር ብቻ የሚያስብ ሰው ሞኝ ነው፤ ብልኅ ግን የሞትንም ነገር ያስባል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው።

Ver Capítulo



መክብብ 7:4
21 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


አክ​ዓ​ብም ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ናቡቴ እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ወደ ናቡቴ ወይን ቦታ ሊወ​ር​ሰው ተነ​ሥቶ ወረደ።


እኔ በልቤ፥ “ና በደ​ስ​ታም እፈ​ት​ን​ሃ​ለሁ፥ እነሆ፥ መል​ካ​ም​ንም እይ” አልሁ፤ ይህም እነሆ፥ ከንቱ ነበረ።


ከሣቅ ኀዘን ይሻ​ላል፥ ከፊት ኀዘን የተ​ነሣ ልብ ደስ ይሰ​ኛ​ልና።


ለሰው የሰ​ነ​ፎ​ችን ዘፈን ከሚ​ሰማ ይልቅ የጠ​ቢ​ባ​ንን ተግ​ሣጽ መስ​ማት ይሻ​ለ​ዋል።


ልቤ ሳተ፤ ኀጢ​አ​ቴም አሰ​ጠ​መኝ፤ ሰው​ነ​ቴም ደነ​ገ​ጠ​ብኝ።


በሞ​ቃ​ቸው ጊዜ እን​ዲ​ዝሉ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እን​ቅ​ልፍ እን​ዲ​ተኙ መጠ​ጥን አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አሰ​ክ​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ነ​ቁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


መሳ​ፍ​ን​ቶ​ች​ዋ​ንና ጥበ​በ​ኞ​ች​ዋ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንና ሹሞ​ች​ዋን፥ ኀያ​ላ​ኖ​ች​ዋ​ንም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አን​ቀ​ላ​ፍ​ተው አይ​ነ​ቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ለው ንጉሥ።


በን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ቀን አለ​ቆች ከወ​ይን ጠጅ ሙቀት የተ​ነሣ ታመሙ፤ እነ​ር​ሱም ከዋ​ዘ​ኞች ጋር እጆ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


አቤ​ግ​ያም ወደ ናባል መጣች፤ እነ​ሆም፥ በቤቱ እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ ያደ​ርግ ነበር፤ ናባ​ልም እጅግ ሰክሮ ነበ​ርና ልቡ ደስ ብሎት ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ታናሽ ነገር ወይም ታላቅ ነገር አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም ነበር።


ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።