መክብብ 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ደዌ ነው፥ እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳልና፥ ለሰውነቱ ለሚደክም ሰው ትርፉ ምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ነው፤ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፤ የሚደክመው ለነፋስ ስለ ሆነ፣ ትርፉ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘመኑን በሙሉ በጨለማ፥ በከባድ ብስጭት፥ በደዌና በቁጣ ይጨርሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራቁቱን እንደ ተወለደ ራቁቱን መሄዱ እጅግ የሚያሳዝን ነው፤ ድካሙ ሁሉ ነፋስን እንደ መጨበጥ ከንቱ ከሆነ ጥቅሙ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፥ እንደ መጣ እንዲሁ ይሄዳል፥ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድር ነው? |
እጄ የሠራቻትን ሥራዬን ሁሉ፥ የደከምሁበትንም ድካሜን ሁሉ ተመለከትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነበረ፥ ከፀሐይ በታችም ትርፍ አልነበረም።
አንተን በመፍራት አቤቱ፥ እኛ ፀንሰናል፤ ምጥም ይዞናል፤ በምድርም የማዳንህን መንፈስ ወለድን፤ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ።
ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፤ ሕጌን የተማሩትም አላወቁኝም፤ ጠባቂዎችም ዐመፁብኝ፤ ነቢያትም በበዐል ትንቢት ተናገሩ፤ የማይጠቅማቸውንም ነገር ተከተሉ።
ነፋስን ዘርተዋልና ዐውሎ ነፋስን አጨዱ፤ ለነዶአቸውም ኀይል የለውም፤ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም ጠላት ይበላዋል።
የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘለዓለም ሕይወት ለሚኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚጠፋው መብል አይደለም፤ ይህን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”