Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አን​ተን በመ​ፍ​ራት አቤቱ፥ እኛ ፀን​ሰ​ናል፤ ምጥም ይዞ​ናል፤ በም​ድ​ርም የማ​ዳ​ን​ህን መን​ፈስ ወለ​ድን፤ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ይወ​ድ​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አረገዝን በምጥም ተጨነቅን፤ ነገር ግን ነፋስን ወለድን፤ ለምድርም ድነትን አላመጣንም፤ የዓለምን ሕዝብ አልወለድንም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፤ በምድርም ደኅንነት አላመጣንም፤ በዓለም እንዲኖሩም ሕዝብ አልወለድንም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤ ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እኛ ፀንሰናል ምጥም ይዞናል፥ ነፋስንም እንደምንወልድ ሆነናል፥ በምድርም ደኅንነት አላደረግነም፥ በዓለምም የሚኖሩ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:18
12 Referencias Cruzadas  

ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።


ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ እና​ትም ለማ​ማጥ ኀይል የላ​ትም።


ዛሬ ታያ​ላ​ችሁ፤ ዛሬ ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ የመ​ን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ኀይል ከንቱ ይሆ​ናል፤ እሳ​ትም ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች።


ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም።


ሳኦ​ልም፦“በዚ​ያች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ድኅ​ነ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ዛሬ አንድ ሰው አይ​ሞ​ትም” አለ።


ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።


ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios