ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
ዘዳግም 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ ከሴቶችህ መካን አትኖርም፤ ልጆች የሌሏት አገልጋይም አትኖርም፤ ከከብትህም መካን አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕዝቦች ሁሉ የበለጠ አንተ ትባረካለህ፤ ከአንተ ወይም ከከብቶችህ መካከል የማይወልድ ወንድ ወይም ሴት አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝቦች ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፥ ወንድ ይሁን ወይም ሴት በሰውህና በከብትህም ዘንድ መካን አይኖርብህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተን ያኽል በብዙ የተባረከ ሕዝብ በዓለም ላይ ከቶ አይገኝም፤ ከአንተ መካከል ወንድም ሆነ ሴት እንዲሁም ከእንስሶችህ መካከል መኻን አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ በሰውህና በከብትህም ዘንድ ወንድ ቢሆን ወይም ሴት ብትሆን መካን አይሆንብህም። |
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
ወደ እናንተም እመለከታለሁ፤ አባዛችኋለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።
አምላክህ እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ከብቶችህን በማብዛት እግዚአብሔር በጎነቱን ያበዛልሃል።
እግዚአብሔርም በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአንተ ደስ ይለዋልና አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ በከብትህም ብዛት እጅግ ይባርክሃል።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”