Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ሲመጣ ያየ​ኸ​ውን ክፉ ሕማ​ምና ደዌ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ያር​ቅ​ል​ሃል፤ ያየ​ኸ​ው​ንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያ​መ​ጣ​ውም፤ ከአ​ን​ተም በሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ ላይ ይመ​ል​ሰ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔር ከማናቸውም በሽታ ነጻ ያደርግሃል፤ በግብጽ የምታውቃቸውን እነዚያን አሠቃቂ በሽታዎች በሚጠሉህ ሁሉ ላይ እንጂ በአንተ ላይ አያመጣብህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር ከበሽታ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ በግብጽ አገር በነበርክ ጊዜ ካየኸው አሠቃቂ በሽታ ሁሉ ማንኛውንም በአንተ ላይ አያመጣም፤ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች በሚጠሉህ ላይ ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግዚአብሔርም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 7:15
9 Referencias Cruzadas  

ቀንዴ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ከፍ ከፍ ይላል፥ ሽም​ግ​ል​ና​ዬም በዘ​ይት ይለ​መ​ል​ማል።


እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ለህ፤ እኔ እህ​ል​ህ​ንና ወይ​ን​ህን፥ ውኃ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤ በሽ​ታ​ንም ከአ​ንተ አር​ቃ​ለሁ።


ጠን​ቋ​ዮ​ችም ቍስል ስለ ነበ​ረ​ባ​ቸው በሙሴ ፊት መቆም አል​ቻ​ሉም፤ ቍስል ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንና ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሁሉ ይዞ​አ​ቸው ነበ​ርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል።


የፈ​ራ​ኸ​ው​ንም የግ​ብፅ ደዌ ሁሉ እን​ደ​ገና ያመ​ጣ​ብ​ሃል፤ ያጣ​ብ​ቅ​ብ​ህ​ማል።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መር​ገም ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህና በሚ​ጠ​ሉህ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ህም ላይ ያመ​ጣ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos