La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 5:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስሙ፤ ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተ ቅረብ፤ አምላካችን ጌታ የሚለውን ሁሉ ስማ፤ አምላካችን ጌታም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተ ቅረብ፥ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔርም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።

Ver Capítulo



ዘዳግም 5:27
11 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን መስ​ክ​ር​ላ​ቸው፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም ሥራ ሁሉ አሳ​ያ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ አንድ ቃል ሆነው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አደ​ረሰ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።


ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።


ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እኛ የላ​ከ​ህን ነገር ሁሉ ባና​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እው​ነ​ተ​ኛና ታማኝ ምስ​ክር ይሁን።


የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ም​ን​ሰማ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አን​ተን ወደ እርሱ የም​ን​ል​ክህ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።


ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው አም​ላ​ክን ድምፅ ሰምቶ በሕ​ይ​ወት የኖረ ማን ነው?


“በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ኝም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ና​ን​ተን ቃል ድምፅ ሰማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ይህ ሕዝብ የተ​ና​ገ​ሩ​ህን ቃል ድምፅ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ የተ​ና​ገ​ሩህ ሁሉ ትክ​ክል ነው።


ወደ መለ​ከት ድም​ፅም፥ ወደ ቃሎ​ችም ነገር አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና፥ ያንም ነገር የሰ​ሙት ሌላ ቃል እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ባ​ቸው ለመኑ።


ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ ቃሉ​ንም እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።