ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፥ “ዐይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ መስዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤
ዘዳግም 34:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር አሳየው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፒስጋ ራስ ወጣ፥ ጌታም እስከ ዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ከሞዓብ ሜዳ በኢያሪኮ ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግዚአብሔርም እስከዳን ድረስ ያለውን የገለዓድን ምድር፥ |
ሎጥ ከተለየው በኋላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፥ “ዐይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ መስዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፤
አብራምም የወንድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ ወገኖቹንና ቤተሰቦቹን ሁሉ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከትሎ አሳደዳቸው።
በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ፤ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ በዚያም ላይ እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር በፊቴ ነበረ።
በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወደዚህ በናባው አሻገር ወዳለው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ይገዙአት ዘንድ እኔ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤
ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ተራራው ራስ ውጣ፤ ዐይንህንም ወደ ባሕር ወደ መስዕም፥ ወደ አዜብም ወደ ምሥራቅም አንሥተህ በዐይንህ ተመልከት።
“በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፤ እነሆም፥ በዐይንህ እንድታያት አደረግሁህ፤ ነገር ግን ወደዚያች አትገባም” አለው።
የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የዳን ልጆችም በተራራው ላይ የሚያስጨንቋቸው አሞሬዎናውያንን አላስጨነቁአቸውም። አሞሬዎናውያንም ወደ ሸለቆዎች ይወርዱ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም። ከእነርሱም ከርስታቸው ዳርቻ አንድ ክፍልን ወሰዱ።
የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፤ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።
በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤
ከተማዪቱንም ከእስራኤል በተወለደው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፤ የከተማዪቱም ስም አስቀድሞ ሌሳ ነበረ።