ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
ዘዳግም 30:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአንተ ደስ ይለዋልና አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ በከብትህም ብዛት እጅግ ይባርክሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉና በወገብህ ፍሬ፣ በእንስሳትህ ግልገሎችና በምድርህ ሰብል እጅግ ያበለጽግሃል። በአባቶችህ ደስ እንደ ተሠኘ ሁሉ፣ እግዚአብሔር አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደገና በአንተ ደስ ይለዋልና፥ ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ እንዲሁም በከብትህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ እጅግ ያበለጽግሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ያበለጽግሃል፤ ልጆችህን፤ እንስሶችህንና የምድርህን ሰብልና ፍሬ ያበዛልሃል፤ እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶችህን በማበልጸግ ደስ ይለው እንደ ነበር አንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ በዚህም ሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ብትጠብቅ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ፥ እግዚአብሔር በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአንተ ደስ ይለዋልና አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ በሆድህም ፍሬ በከብትህም ፍሬ በእርሻህም ፍሬ እጅግ ይባርክሃል። |
ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤትን አደርጋለሁ፤ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ በውስጥዋ አይሰማም።
እንዲህም ይሆናል፤ አፈርሳቸውና ክፉ አደርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፥ እንዲሁ እሠራቸውና እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ፥ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ፥ ለክብርና ለገናንነት ትሆናለች።”
በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ የሚያስፈራችሁም የለም፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ።
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
እግዚአብሔርም በጎ ያደርግልህ ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል፤ ትወርሳትም ዘንድ ከምትገባባት ምድር ትነቀላለህ ።
አንተም ተመልሰህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ትሰማለህ፤ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዙን ሁሉ ታደርጋለህ።
ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ ከሴቶችህ መካን አትኖርም፤ ልጆች የሌሏት አገልጋይም አትኖርም፤ ከከብትህም መካን አይኖርም።