እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፥ “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን እንዳይመልሱ ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ” ካላቸው ከአሕዝብ አገባ፤ ሰሎሞን ግን እነርሱን ተከተለ፤ ወደዳቸውም።
ዘዳግም 30:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብህ ግን ቢስት፥ አንተም ባትሰማ፥ ብትታለልም፥ ለሌሎች አማልክትም ብትሰግድ፥ ብታመልካቸውም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳሩ ግን ልብህ ወደ ኋላ ቢመለስና ባትታዘዝ፣ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለልና ብታመልካቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብህ ግን ርቆ አንተም ባትሰማ፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድላቸውና ብታመልካቸው ግን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ልብህን ከእግዚአብሔር አርቀህ ቃሉን የማትሰማ ብትሆን፥ ለሌሎችም አማልክት ልትሰግድላቸውና ልታመልካቸው ብትባክን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብህ ግን ቢስት አንተም ባትሰማ፥ ብትታለልም፥ ለሌሎችም አማልክት ብትሰግድ ብታመልካቸውም፥ |
እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፥ “አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን እንዳይመልሱ ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ” ካላቸው ከአሕዝብ አገባ፤ ሰሎሞን ግን እነርሱን ተከተለ፤ ወደዳቸውም።
ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም ተጠንቀቁ።
ዛሬ እኔ የማዝዝህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ብትሰማ፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም ብትወድድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ብትሄድ፥ ሥርዐቱንና ፍርዱንም ብትጠብቅ በሕይወት ትኖራለህ፤ በቍጥርም ትበዛለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ልትወርሳት በምትሄድባት በምድሪቱ ሁሉ ይባርክሃል።
ፈጽመህ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬ እነግርሃለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ ትወርሳት ዘንድ በምትገባባት ምድር ዘመንህ አይረዝምም።
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ዕወቁ፤ ከእናንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይማኖት የጐደለውና ተጠራጣሪ፥ ከሕያው እግዚአብሔር የሚለያችሁ ክፉ ልብ አይኑር።
በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች፥ ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ ደረሱ፤ እንዲህም ብለው ነገሩአቸው