ወደ እኔ ብትመለሱ ግን፥ ትእዛዜንም ብትጠብቁ፥ ብታደርጓትም ምንም ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበተኑ፥ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።
ዘዳግም 30:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙን፥ ሥርዐቱንና ፍርዱን ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ ይባርክሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሚሆነው፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ስትመለስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፥ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ለመጠበቅ፥ በፍጹምም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ ጌታ ወደ አምላክህ ተመለስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የሚያደርገው በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን ትእዛዞችና ሕጎች በመጠበቅ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር የተመለስክ እንደ ሆነ ነው። |
ወደ እኔ ብትመለሱ ግን፥ ትእዛዜንም ብትጠብቁ፥ ብታደርጓትም ምንም ከእናንተ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢበተኑ፥ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ስሜም ይኖርበት ዘንድ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።
“ኀጢአተኛውም ከአደረጋት ኀጢአት ሁሉ ቢመለስ፥ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ፥ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።
እኔ ሕያው ነኝና ኀጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።
አስቀድሜ በኢየሩሳሌምና በደማስቆ ላሉት፥ ለይሁዳ አውራጃዎችም ሁሉ ነገርኋቸው፤ ለአሕዛብም ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ፥ ለንስሓቸውም የሚገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስተማርኋቸው።
እግዚአብሔርም በዚህ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው እንደ ቃል ኪዳኑ ርግማን ሁሉ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።
ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔርም ተመለስ፤ እኔም ዛሬ እንደማዝዝህ ሁሉ አንተና ልጆችህ በፍጹም ልብና በፍጹም ነፍስ ቃሉን ስማ፤
አንተም ተመልሰህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ትሰማለህ፤ ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዙን ሁሉ ታደርጋለህ።
ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በመከራህም ጊዜ በልብህም ሁሉ፥ በነፍስህም ሁሉየፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።