Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 29:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ቃል ኪዳኑ ርግ​ማን ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ለጥ​ፋት ይለ​የ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት፣ እግዚአብሔር እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት ጌታ እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር እንደዚህ ያለውን ሰው በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የእርግማን ቃል ኪዳን መሠረት ከእስራኤል ነገዶች መካከል አውጥቶ ያጠፋዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔርም በዚህ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው እንደ ቃል ኪዳኑ እርግማን ሁሉ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 29:21
12 Referencias Cruzadas  

እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤


ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።


እጄም ሐሰ​ተኛ ራእ​ይን በሚ​ያዩ፥ ሕዝ​ቤ​ንም ለማ​ታ​ለል በከ​ንቱ በሚ​ያ​ም​ዋ​ርቱ ነቢ​ያት ላይ ትሆ​ና​ለች። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝቤ ማኅ​በር ውስጥ አይ​ኖ​ሩም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መጽ​ሐፍ አይ​ጻ​ፉም፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አይ​ገ​ቡም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ትእ​ዛ​ዙን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱን ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ፥ በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለስ ይባ​ር​ክ​ሃል።


ለመ​ከራ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ንም እጨ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ቍጣ​ዬና መቅ​ሠ​ፍቴ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እን​ዲሁ ወደ ግብፅ በገ​ባ​ችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈ​ስ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ እና​ን​ተም ለጥ​ላ​ቻና ለጥ​ፋት ለስ​ድ​ብና ለር​ግ​ማን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይች​ንም ስፍራ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ዩ​አ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም መቅ​ሠ​ፍት፥ ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ለብዙ ጊዜ የሚ​ኖር ክፉ ደዌና ሕማ​ምን ሁሉ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


ደግ​ሞም ይህ ሕግ ባለ​በት መጽ​ሐፍ ውስጥ ያል​ተ​ጻ​ፈ​ውን ደዌ ሁሉ፥ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ንም ሁሉ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios