Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 30:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህንንም የሚያደርገው በዚህ የሕግ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን ትእዛዞችና ሕጎች በመጠበቅ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር የተመለስክ እንደ ሆነ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህም የሚሆነው፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ከታዘዝህና በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዐቱን በመጠበቅ፣ በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ስትመለስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፥ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ለመጠበቅ፥ በፍጹምም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ወደ ጌታ ወደ አምላክህ ተመለስ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ትእ​ዛ​ዙን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱን ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ፥ በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለስ ይባ​ር​ክ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 30:10
17 Referencias Cruzadas  

በዚያም ስትኖሩ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትናፍቃላችሁ፤ እርሱንም በሙሉ ልባችሁ ብትሹት ታገኙታላችሁ፤


መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ዋጋ የለውም፤ ዋናው ነገር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ነው።


አንተም እንደገና ለእርሱ ታዛዥ ትሆናለህ፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህንም የእርሱን ትእዛዞች ትጠብቃለህ፤


አንተ ከዘሮችህ ጋር ወደ እግዚአብሔር ብትመለስና ዛሬ እኔ ለምሰጥህ ለእግዚአብሔር ሕጎች ከልብ ታዛዥ ሆነህ ብትገኝ፥


ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ያሉት ሰዎች፥ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ያሉት እንዲሁም አሕዛብ ጭምር ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ አስተማርኳቸው፤ ንስሓ መግባታቸውን የሚያመለክት ነገር እንዲያደርጉም አስተማርኳቸው።


እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስላችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፤


ክፉም ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ በእርሱ ይኖራል።


አንድን ክፉ ሰው በእርግጥ እንደሚሞት ባስታውቀውና እርሱ ግን ኃጢአት መሥራቱን ትቶ ሕጋዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥


እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ኃጢአተኛ ሰው፥ ኃጢአት መሥራቱን ትቶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ በኃጢአቱ እንዲሞት አልፈቅድም፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! ክፉ ሥራችሁን ተዉ፤ መሞትን ለምን ትፈልጋላችሁ? ብለህ ንገራቸው።


“ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ ሕጌን ቢጠብቅ፥ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤


እግዚአብሔር እንደዚህ ያለውን ሰው በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የእርግማን ቃል ኪዳን መሠረት ከእስራኤል ነገዶች መካከል አውጥቶ ያጠፋዋል።


“ዛሬ እኔ የምሰጥህ ትእዛዝ በጣም ከባድ ወይም ከአንተ የራቀ አይደለም፤


እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኀይልህ ውደድ፤


በዚያን ጊዜ በሩቅ የሚኖሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲታደስ ለመርዳት ይመጣሉ። ቤተ መቅደሱ በታደሰ ጊዜ እኔን ወደ እናንተ የላከኝ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቃላችሁ። ይህም ሁሉ የሚፈጸመው ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቃል ፍጹም ታዛዦች የሆናችሁ እንደ ሆነ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios