ዘዳግም 29:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ዓመት በምድረ በዳ መራችሁ፤ ልብሳችሁም አላረጀባችሁም፤ ጫማችሁም በእግራችሁ ላይ አልተቀደደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ በመራኋችሁ በእነዚያ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብሳችሁ አላረጀም፤ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ስመራችሁ ልብሳችሁ አላረጀም፤ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ስመራችሁ ልብሳችሁ አላረጀም፤ ጫማችሁም አላለቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ዓመት በምድረ በዳ መራኋችሁ፤ ልብሳችሁም አላረጀባችሁም፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ላይ አላረጀም። |
ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይቅበዘበዛሉ፤ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ግልሙትናችሁን ይሸከማሉ።
በአርባኛው ዓመት በዐሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን፥ ሙሴ እንዲነግራቸው እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤
አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ።
ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፤ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና መገበህ።
እነዚህም የጠጅ ረዋቶች አዲሶች ሳሉ ሞላንባቸው፤ እነሆም፥ አርጅተው ተቀድደዋል፤ መንገዳችንም እጅግ ስለ ራቀብን እነዚህ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።”
በእግራቸውም ያደረጉት ጫማ ያረጀና ማዘቢያው የተበጣጠሰ፥ ልብሳቸውም በላያቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀ፥ የሻገተና የተበላሸ ነበረ።