የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ መውጫህንና መግቢያህንም ያውቅ ዘንድ ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን?” አለው።
ዘዳግም 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትገባ ትባረካለህ፤ ስትወጣም ትባረካለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስትገባ ትባረካለህ፤ ስትወጣም ትባረካለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር መግባትህንና መውጣትህን ይባርክልሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በመግባትህ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በመውጣትህም ቡሩክ ትሆናለህ። |
የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ መውጫህንና መግቢያህንም ያውቅ ዘንድ ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን?” አለው።
አሁንም በዚህ ሕዝብ ፊት እወጣና እገባ ዘንድ ጥበብንና ማስተዋልን ስጠኝ፤ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ መፍረድ የሚቻለው የለምና።”
በፊታቸው የሚወጣውንና የሚገባውን፥ የሚያስወጣቸውንና፥ የሚያስገባቸውንም፥ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን።”
“እግዚአብሔርም ከእግርህ በታች ይወድቁ ዘንድ የሚቃወሙህን ጠላቶችህን በእጅህ ይጥላቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፤ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ።
አላቸውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ‘ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል።