ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
ዘዳግም 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም መንጋ፥ የበግህም መንጋ ቡሩክ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማሕፀንህ ፍሬ፣ የምድርህ አዝመራ፣ የእንስሳትህ ግልገሎች፣ የከብትህ ጥጃ፣ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የማሕፀንህ ፍሬ፥ የምድርህ አዝመራ፥ የእንስሳትህ ግልገሎች፥ የከብትህ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ልጆችህን፥ የምድር ፍሬህን፥ የቀንድ ከብትህን፥ የበግንና የፍየል መንጋህን ይባርክልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆድህ ፍሬ፥ የምድርህም ፍሬ፥ የከብትህም ፍሬ፥ የላምህም ርቢ፥ የበግህም ርቢ ቡሩክ ይሆናል። |
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን ቤት በዮሴፍ ምክንያት ባረከው። የእግዚአብሔርም በረከት በቤቱም፥ በእርሻውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
ወደ እናንተም እመለከታለሁ፤ አባዛችኋለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርጋችኋለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።
አምላክህ እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ከብቶችህን በማብዛት እግዚአብሔር በጎነቱን ያበዛልሃል።
ይወድድህማል፤ ይባርክህማል፤ ያባዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ፥ የመሬትህንም ፍሬ፥ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የከብትህንም ብዛት፥ የበግህንም መንጋ ይባርክልሃል።
ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።