ዘዳግም 28:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እስክትጠፋ ድረስ በሚቀሥፍ ደዌ፣ ትኵሳትና ዕባጭ፣ ኀይለኛ ሙቀትና ድርቅ፣ ዋግና አረማሞ ይመታሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እስክትጠፋ ድረስ በሚቀሥፍ በሽታ ንዳድና ዕባጭ፥ ኀይለኛ ሙቀትና ድርቅ፥ ዋግና አረማሞ ይመታሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሚያመነምን በሽታ፥ በትኲሳት፥ በቊስል፥ በኀይለኛ ሙቀትና በድርቅ እስክትጠፋም ድረስ ይመታሃል። ሰብልህንም ለማጥፋት ዋግና አረማሞ ይልክብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኩሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል። |
“በምድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ ቢሆን፥ አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢመጣ፥ የሕዝብህም ጠላት ከከተሞቻቸው በአንዲቱ ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
“በምድር ላይ ራብ፥ ወይም ቸነፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረማሞ፥ ወይም አንበጣ፥ ወይም ኩብኩባ ቢሆን፥ ጠላቶቻቸውም የሀገሩን ከተሞች ከብበው ቢያስጨንቁአቸው፥ ማናቸውም መቅሠፍትና ደዌ ቢሆን፥
ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ቢያቀርቡም ደስ አልሰኝባቸውም፤ በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ።”
“በክፉ ሞት ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩምም፤ ነገር ግን በመሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ በራብም ይጠፋሉ፤ ሬሳዎቻቸውም ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት መብል ይሆናሉ።”
እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሀትን፥ ክሳትንም፥ ዐይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያጠፋ ትኩሳት አወርድባችኋለሁ፤ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
በአባርና በቸነፈር መታኋችሁ፤ አትክልታችሁ፥ ወይናችሁና በለሳችሁ፥ ወይራችሁም ከበጀ በኋላ ተምች በላው፤ ይህም ሆኖ እናንተ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር።
እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።
እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ።
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።