ዘዳግም 24:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሃ ነውና፥ ተስፋውም እርሱ ነውና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ፥ ኀጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሠራበትን ሒሳብ በዕለቱ፣ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጕጕት ይጠባበቀዋልና። አለዚያ ወደ እግዚአብሔር ይጮኽና ኀጢአት ይሆንብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራበትን ሒሣብ በዕለቱ፥ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋል። ያለበለዚያ ወደ ጌታ ይጮኽና ኃጢአት ይሆንብሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ድኻ በመሆኑ ያን ገንዘብ ለማግኘት በብርቱ ጒጉት ስለሚጠብቅ በየቀኑ የሠራበትን ገንዘብ ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ስጠው፤ ባትከፍለው ግን ወደ እግዚአብሔር በመጮኽ ያሳጣሃል፤ አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሀ ነውና፥ ነፍሱም ጠንክራ ትፈልገዋለችና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ ኃጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው። |
ወይም ጌታውን እንደሚፈራ አገልጋይ ጥላውንም እንደሚመኝ፥ ወይም ደመወዙን እንደሚጠብቅ ምንደኛ አይደለምን?
የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
ቤቱን በዐመፅ፥ አዳራሹንም ያለ እውነት ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው ወዮለት!
“ከአንተ ጋር ያለው ወንድምህ ቢደኸይ፥ እጁም በአንተ ዘንድ ቢደክም እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛ ትረዳዋለህ፤ ከአንተም ጋር ይኑር።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል።