ዘዳግም 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴይርን ተራራ ለዔሳው ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳን አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከየትኛውም ምድራቸው ላይ ለጫማችሁ መርገጫ ታኽል እንኳ መሬት ስለማልሰጣችሁ፣ ለጦርነት አታነሣሧቸው። ኰረብታማውን የሴይርን አገር ርስት አድርጌ ለዔሳው ሰጥቼዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው። |
ምድሪቱን፥ በምድር ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኀይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ፤ ለዐይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
በውስጥዋም አንድ ጫማ ታህል ስንኳን ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን እርሱ ከእርሱም በኋላ ዘሩ ሊገዛት ልጅ ሳይኖረው ያንጊዜ እርስዋን ያወርሰው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።
ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እነርሱ ወረሱአቸው፤ በእነርሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።
ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው።