ዘዳግም 2:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ በእጃችን ሰጠን፤ እርሱንም፥ ልጆቹንም፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላካችን እግዚአብሔር በእጃችን ላይ ጣለው፤ እኛም፣ እርሱን ከወንድ ልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድ ላይ መታነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችንም እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ መታን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እጅ ስለ ጣለው እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ሰው ሁሉ ገደልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችንም እግዚአብሔር እርሱን አሳልፎ ሰጠን፤ እርሱንም ልጆቹንም ሕዝቡንም ሁሉ መታን። |
ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አሰፋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከአንተም አስወጣቸዋለሁ።
እስራኤልም በሰይፍ መታው፤ ምድሩንም ከአርኖን ጀምሮ እስከ አሞን ልጆች እስከ ያቦቅ ድረስ ወረሰ፤ የአሞንም ልጆች ዳርቻ ኢያዜር ነበረ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ እንጀራ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክረውን መጠጥም አልጠጣችሁም።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
ይሁዳም ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ገደለባቸው።
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፥ “ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፤ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።”