መሳፍንት 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ይሁዳም ወጣ፤ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዜዎናውያንን በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎችን ገደለባቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ይሁዳ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ወጣ፤ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ ቤዜቅ በተባለውም ስፍራ ዐሥር ሺሕ ሰው ገደሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከዚያ በኋላ ይሁዳ ሕዝብ ዘመተ፤ ጌታም ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በቤዜቅም ዐሥር ሺህውን ድል ነሡ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከዚያ በኋላ የይሁዳ ሕዝብ አብሮ ዘመተ። እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፈሪዛውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው፤ እነርሱም በቤዜቅ ዐሥር ሺህ ሠራዊትን መቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ይሁዳም ወጣ፥ እግዚአብሔርም ከነዓናውያንንና ፌርዛውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፥ ከእነርሱም በቤዜቅ ውስጥ አሥር ሺህ ሰዎች ገደሉ። Ver Capítulo |