ዘዳግም 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንድሙ ላይ ክፋትን ያደርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእርሱ ላይ ታደርጉበታላችሁ፤ እንዲሁም ከእናንተ መካከል ክፉውን ታስወግዳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በርሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለተከሳሹ ታስቦ የነበረውን ቅጣት እርሱ ይቀበላል፤ ይህን የመሰለ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ዐይነት ታስወግዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንድሙ ላይ ያደርገው ዘንድ ያሰበውን በእርሱ ላይ ትመልሱበታላችሁ፤ እንዲሁም ከአንተ መካከል ክፋቱን ታስወግዳለህ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት ስላላክኋቸው፦ በዚህች ሀገር ሰይፍና ረሃብ አይሆንም ስለሚሉ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ “እነዚያ ነቢያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ።
“ማንም ሰው ከእስራኤል ልጆች ከወንድሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰርቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰረቀውን ሰው ይግደሉት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ።