ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።
ዘዳግም 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባት ቀንም በሀገርህ ሁሉ የቦካ አይታይም፤ በመጀመሪያው ቀን ማታ ከሠዋኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይደር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማንኛውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቈይ አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርህ ሁሉ ላይ በአንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዋውም ላይ ማናቸውንም ሥጋ ጧት ድረስ እንዲቆይ አታድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ሰባት ቀን ድረስ በምድርህ በማንኛውም ሰው ቤት እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ቀን ማታ ለመሥዋዕት የታረደው እንስሳ ሥጋው በሙሉ በዚያው ሌሊት ተበልቶ ማለቅ አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀንም በአገርህ ሁሉ እርሾ አይታይም፤ በመጀመሪያው ቀን ማታ ከሠዋኸው ሥጋ እስከ ነገ ድረስ ምንም አይደር። |
ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።
“ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያም ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታወጣላችሁ፤ ከመጀመሪያውም ቀን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የሚበላ ነፍስ ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ።
ሰባት ቀንም ሙሉ ቂጣ ትበላላችሁ፤ በእናንተም ዘንድ እርሾ ያለበት እንጀራ አይታይ፤ በአውራጃዎቻችሁ ሁሉ እርሾ አይኑር።
ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”