ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
ዘዳግም 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ ዐስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም ራስህ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህና አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ይህን ትእዛዝ ዛሬ የምሰጥህም በዚሁ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ራስህ በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክና ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም በግብጽ ምድር ባሪያ እንደ ነበርክና እግዚአብሔር አምላክህ ነጻ ያወጣህ መሆኑን አስታውስ፤ እኔም ዛሬ ይህን ትእዛዝ የማዝህ በዚህ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ አምላክህም እግዚአብሔር እንዳዳነህ አስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ። |
ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ታላቅ ስምን ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና ሰፈሮቻቸውን በመበተን ከግብፅ በተቤዠኸው ሕዝብህ ፊት ታምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ መራው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?
እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፥ ስሙኝ፤ የተቈረጣችሁበትን ጽኑዕ ዓለት የተቈፈራችሁባትንም ጥልቅ ጕድጓድ ተመልከቱ።
ስለዚህ እነሆ፥ “የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤
ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር።
ነገር ግን ከበጎችህ፥ ከእህልህም፥ ከወይንህም መጭመቂያ ስንቅ ትሰንቅለታለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።