የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ።
ዘዳግም 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና በድንጋይ ይውገሩት፤ ይግደሉትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጓልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከጌታ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጎአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባርነት ከኖርክበት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ስለ ሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። |
የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበሩት፤ መሠዊያዎቹንም አፈረሱ፤ ምስሎቹንም አደቀቁ፥ የበዓልንም ካህን ማታንን በመሠዊያው ፊት ገደሉት። ካህኑ ዮዳሄም ለእግዚአብሔር ቤት ጠባቂዎችን ሾመ።
እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፤ ሂዱና በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፤ እያንዳንዱም ወንድሙን፥ እያንዳንዱም ጎረቤቱን፥ እያንዳንዱም የቅርቡን ይግደል” አላቸው።
“ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የሀገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገሩት።
“ወንድ ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይም ይውገሩአቸው፤ በደለኞች ናቸውና።”
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ ተሳዳቢውንም ከሰፈር ወደ ውጭ አወጡት፤ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትመትዋቸዋላችሁ።
እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
የከተማዉም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ደብድበው ይግደሉት፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፤ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።
ወደ ሰማይ አትመልከት፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን፥ ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ አይተህ፥ ሰግደህላቸው፥ አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ።
ኢያሱም፥ “ለምን አጠፋኸን? ዛሬ እንዳጠፋኸን እግዚአብሔር ዛሬ ያጥፋህ” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉት፤ በድንጋይም ወገሩአቸው።