በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
አሞጽ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ አዝዛለሁ፤ እህልም በመንሽ እንደሚዘራ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እዘራለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣ የእስራኤልን ቤት፣ በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንደሚነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ በሕዝቦች መካከል እንዲበተኑ አዛለሁ፤ የሚበተኑትም እህል በወንፊት እንደሚነፋ ዐይነት ነው፤ ነገር ግን ወንፊቱ ሲነቃነቅ ገለባው እንጂ አንድም ቅንጣት አይበተንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንዲነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፥ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም። |
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
እስትንፋሱም አሕዛብን ስለ ከንቱ ስሕተታቸው ሊከፋፍላቸው በሸለቆ እንደሚያጥለቀልቅ፥ እስከ አንገትም እንደሚደርስና እንደሚከፋፍል ውኃ ይጐርፋል፤ ስሕተታቸውም ይከተላቸዋል፤ ይወስዳቸዋልም።
“ይህ ሕግ ከፊቴ ቢወገድ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘለዓለም ይቀራል።”
አንተ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም ያሳደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።”
ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይደርሱበት ሕዝብ አይገኝም።
ከእናንተም ዘንድ ዐመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ፤ ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ወደ አሕዛብም በተንኋቸው፤ ወደ ሀገሮችም ዘራኋቸው፤ እንደ መንገዳቸውና እንደ በደላቸውም መጠን ፈረድሁባቸው።
እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አላስቀርም፤
ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፤ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ።
ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፤ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፤ በኋላቸውም ሰይፍን እመዝዛለሁ።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን ታመልካለህ።