La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




አሞጽ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ቹን ከመ​ከ​ተል ወሰ​ደኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሂድ፥ ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ትን​ቢት ተና​ገር አለኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም በጎቹን ከመከተል ወሰደኝ፥ ጌታም፦ “ሂድ፥ ለሕዝቤም ለእስራኤል ትንቢት ተናገር” አለኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ ‘ሂድ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ ብሎ ያዘዘኝ ራሱ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በጎቹን ከመከተል ወሰደኝ፥ እግዚአብሔርም፦ ሂድ፥ ለሕዝቤም ለእስራኤል ትንቢት ተናገር አለኝ።

Ver Capítulo



አሞጽ 7:15
15 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤


ከዚ​ያም ሄደ፤ የሣ​ፋ​ጥ​ንም ልጅ ኤል​ሳ​ዕን በዐ​ሥራ ሁለት ጥማድ በሬ​ዎች ሲያ​ርስ፥ እር​ሱም ከዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ጋር ሆኖ አገ​ኘው። ኤል​ያ​ስም ወደ እርሱ አልፎ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን ጣለ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ​ም​ል​ክህ ሁሉ ዘንድ ትሄ​ዳ​ለ​ህና፥ የማ​ዝ​ዝ​ህ​ንም ሁሉ ትና​ገ​ራ​ለ​ህና፦ ሕፃን ነኝ አት​በል።


ኤር​ም​ያ​ስም ለአ​ለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “በሰ​ማ​ች​ሁት ቃል ሁሉ፥ በዚች ቤትና በዚ​ህች ከተማ ላይ ትን​ቢት እና​ገር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ኛል።


አን​በ​ሳው አገሣ፤ የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፤ ትን​ቢት የማ​ይ​ና​ገር ማን ነው?


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”


እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።”


“ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”


ቀድ​ሞም የሚ​ያ​ው​ቁት ሁሉ በነ​ቢ​ያት መካ​ከል ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “በቂስ ልጅ ላይ የሆ​ነው ምን​ድን ነው? በውኑ ሳኦል ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” ተባ​ባሉ።