አሞጽ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ በአሕዛብ ፊትና በደማስቆ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣ ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣ እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው ጫፍ ላይ፣ በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣ እስራኤላውያን ይድናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ከድንክ አልጋና ከአልጋ የእግር ቁራጭ ጋር ይድናሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሰማርያ የሚኖሩ እስራኤላውያን ከአልጋና ከድንክ አልጋ ቊራጭ ጋር ያመልጣሉ፤ ይኸውም እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ ሁለት እግርና የጆሮ ቊራጭ ለማስጣል እንደሚችለው ዐይነት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግርን ወይም የጆሮን ጫፍ እንደሚያድን፥ እንዲሁ በሰማርያ በአልጋ ማዕዘን፥ በደማስቆም በምንጣፍ ላይ የተቀመጡት የእስራኤል ልጆች ይድናሉ። |
የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ ወደ ደማስቆ ወጣ፤ ያዛትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።
በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔምም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም አዝዞአልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
ከዝሆን ጥርስ በተሠራ አልጋ ላይ ለሚተኙ፥ በምንጣፋቸው ደስ ለሚሰኙ፥ ከበጎችም መንጋ ጠቦትን፥ ከጋጥም ውስጥ ጥጃን ለሚመገቡ፥
እነሆ የጌታ የእግዚአብሔር ዐይኖች በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ፤ ነገር ግን የያዕቆብን ቤት ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር።