አሞጽ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሮጥ ሰው ማምለጥ አይችልም፤ ኀይለኛውም በብርታቱ አይዝም፤ አርበኛውም ነፍሱን አያድንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈጣኑ አያመልጥም፤ ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ ኀያሉም ነፍሱን አያድንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጣኑ ሯጭ መሸሽ ሳይችል ይጠፋል፥ ብርቱውም በብርታቱ አይበረታም፥ ኃያሉም ነፍሱን አያድንም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈጣኑ ሯጭ መፍጠን ያቅተዋል፤ ብርቱ ሰዎችንም ኀይላቸው ይከዳቸዋል፤ ጦረኞችም ራሳቸውን ማዳን አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከርዋጪም ሽሽት ይጠፋል፥ ብርቱውም በብርታቱ አይበረታም፥ ኃያሉም ነፍሱን አያድንም፥ ቀስተኛውም አይቆምም፥ |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ሰልፈኞቹም ሁሉ በአዩአቸው ጊዜ፥ በሌሊት ሸሹ፤ በንጉሡም አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል በነበረው ደጅ ከከተማዪቱ ወጡ፤ በዓረባም መንገድ ወጡ።