በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ሐዋርያት ሥራ 9:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሳርያ አወረዱት፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ ላኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ፣ ወደ ቂሳርያ አውርደው ወደ ጠርሴስ ሰደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ወሰዱት፤ ወደ ጠርሴስም ሰደዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ወሰዱት፤ ከዚያም ወደ ጠርሴስ እንዲሄድ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ ወደ ቂሣርያ ወሰዱት ወደ ጠርሴስም ሰደዱት። |
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብረውት መጥተው ነበርና ፈጥነው ይከተሉት ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ላካቸው፤ ተመልሰውም ሄዱ።
በዚያም ወንድሞችን አግኝተን ተቀበሉን፤ በእነርሱ ዘንድም ሰባት ቀን እንድንቀመጥ ለመኑን፤ ከዚያም በኋላ ሄደን ወደ ሮሜ ደረስን።
ፊልጶስም አዛጦን ወደምትባል ሀገር ደረሰ፤ በከተማዎችም ሁሉ እየተዘዋወረ ወደ ቂሳርያ እስኪደርስ ድረስ ያስተምር ነበር።
ጌታም፥ “ተነሣና ቅን በምትባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ከጠርሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸልያልና” አለው።