La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ሴኬ​ምም አፍ​ል​ሰው አብ​ር​ሃም ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በገ​ን​ዘቡ በገ​ዛው መቃ​ብር ቀበ​ሩ​ዋ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አስከሬናቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ፣ አብርሃም ከዔሞር ልጆች ላይ በጥሬ ብር በገዛው መቃብር ተቀበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐጽማቸው ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ተቀበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 7:16
11 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም የኤ​ፍ​ሮ​ንን ነገር ሰማ፤ አብ​ር​ሃ​ምም በኬጢ ልጆች ፊት የነ​ገ​ረ​ው​ንና ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለ​ውን ግብዝ ያይ​ደለ አራት መቶ ምዝ​ምዝ ብር መዝኖ ለኤ​ፍ​ሮን ሰጠው።


“እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ ስደ​ተ​ኛና መጻ​ተኛ ነኝ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ድ​ገዛ የመ​ቃ​ብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳ​ዬ​ንም እንደ እና​ንተ ልቅ​በር።”


ራሔ​ልም ሞተች፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም በም​ት​ወ​ስድ መን​ገድ ተቀ​በ​ረች፤ እር​ስ​ዋም ቤተ ልሔም ናት።


ከአ​ባ​ቶ​ችም ጋር በአ​ን​ቀ​ላ​ፋሁ ጊዜ ከግ​ብፅ ምድር አው​ጥ​ተህ ትወ​ስ​ደ​ኛ​ለህ፤ በአ​ባ​ቶ​ችም መቃ​ብር ትቀ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።” እር​ሱም፥ “እንደ ቃልህ አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ማል​ልኝ” አለው።


ልጆ​ቹም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ደ​ዚ​ያው አደ​ረ​ጉ​ለት፤


ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት።


ሙሴም የዮ​ሴ​ፍን ዐጽም ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መጐ​ብ​ኘ​ትን በጐ​በ​ኛ​ችሁ ጊዜ ዐጽ​ሜን ውሰዱ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ያወ​ጡ​ትን የዮ​ሴ​ፍን አፅም ያዕ​ቆብ በሰ​ቂማ ከሚ​ኖሩ ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን በመቶ በጎች በገ​ዛው ለዮ​ሴፍ ድርሻ አድ​ርጎ በሰ​ጠው እርሻ በአ​ንዱ ክፍል በሰ​ቂማ ቀበ​ሩት።