ሐዋርያት ሥራ 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅና በከነዓን ሀገር ሁሉ ረኃብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉት አጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚያ ጊዜም በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ታላቅ መከራን ያስከተለ ራብ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉትን ዐጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ላይ ታላቅ ችግር ያስከተለ ራብ ሆነ፤ አባቶቻችንም ምግብ ሊያገኙ አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፥ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም። |
በዚያም አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና፤
ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፥ “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፤ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለምና፤ ራብም በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፤ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንቀመጥ።”