እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድርጊልኝ፤ በገባንበት ሀገር ሁሉ ወንድሜ ነው በዪ።’ ”
ሐዋርያት ሥራ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጴጥሮስም፥ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን መንፈስ ትፈታተኑት ዘንድ እንዴት ተባበራችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግሮች በበር ናቸው፤ አንቺንም ይወስዱሻል” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጴጥሮስም፣ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ እንዴት እንዲህ ተስማማችሁ? እነሆ፤ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች ተመልሰው እግራቸው ደጃፍ ላይ ነው! አንቺንም ይዘው ይወጣሉ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጴጥሮስም “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው፤ አንቺንም ያወጡሻል፤” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጴጥሮስም፦ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል” አላት። |
እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፥ ‘ይህን ጽድቅ አድርጊልኝ፤ በገባንበት ሀገር ሁሉ ወንድሜ ነው በዪ።’ ”
ኤልሳዕ ግን በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ከእርሱ ጋር ተቀምጠው ነበር፤ ንጉሡም በፊቱ ከሚቆሙት አንድ ሰው ላከ፤ መልእክተኛውም ገና ሳይደርስ ለሽማግሌዎች፥ “ይህ የነፍሰ ገዳይ ልጅ ራሴን ይቈርጥ ዘንድ እንደ ላከ እዩ፤ መልእክተኛውም በመጣ ጊዜ ደጁን ዘግታችሁ ከልክሉት፤ በደጅም ይቆም ዘንድ ተዉት፤ የጌታው የእግሩ ኮቴ በኋላው ነው” አላቸው።
ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፥ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው።
ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፥ “እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን? ወይስ አይደለም?” ሲሉ እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም “መንሱት” ደግሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥
ጌታውም ጠርቶ፦ ‘በአንተ ላይ የምሰማው ይህ ነገር ምንድን ነው? እንግዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው።
አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ?
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንደ ተፈታተኑት፥ ነዘር እባብም እንደ አጠፋቸው እግዚአብሔርን አንፈታተን።