እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ሐዋርያት ሥራ 4:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅህና ምክርህ እንዲደረግ የወሰኑትን ይፈጽሙ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈጸም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤ |
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል።
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክርን ከሚመክር በግብሩም ገናና ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል። እናንተ ግን ከንቱ መጽናናትን ታበዙ ዘንድ ትሻላችሁ።
“እኔ ጥንት የሠራሁትን አልሰማህምን? እኔ በቀድሞ ዘመን እንዳደረግሁት፥ አሁንም አሕዛብን በምሽጎቻቸው፥ በጽኑ ከተሞቻቸው የሚኖሩትንም ያጠፉ ዘንድ አዘዝሁ።
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።
እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት።
ስለዚህም እግዚአብሔር ተስፋውን ለሚወርሱ ሰዎች ምክሩን እንደማይለውጥ ሊገልጥ ወደደ፤ እንደማይለውጥም በመሓላ አጸናው።