ሐዋርያት ሥራ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም እንል ዘንድ አንችልም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፤” አሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር አንቈጠብም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” አሉአቸው። |
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፥ “ወደምልክህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና፦ ሕፃን ነኝ አትበል።
እኔም እንዲህ አልሁ፥ “የእግዚአብሔርን ስም አላነሣም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በስሙ አልናገርም፥” በአጥንቶች ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፤ መሸከምም አልቻልሁም።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
ስለዚህ ቍጣዬን መላሁባቸው፤ ታገሥሁ፤ ፈጽሜም አላጠፋኋቸውም፤ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጐልማሶችም ጉባኤ ላይ መዓቴን በአንድነት አፈስስባቸዋለሁ፤ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና።
ተነሥተህም ወደ ተማረኩ ወደ ወገንህ ልጆች ሂድ፤ እነርሱም ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው” አለኝ።
በለዓምም ባላቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያደርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ” አለው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤዉ ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል።”
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።”
ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ ጳውሎስ፥ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ቃሉን በማስተማር ይተጋ ነበር።
ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ።