ሐዋርያት ሥራ 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልኮም ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ እንዲያስመጣውና እንዲሰጣቸው ለመኑት፤ እነርሱ ግን ወደዚያ ሄደው በመንገድ ሸምቀው ሊገድሉት ፈልገው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጳውሎስን መንገድ ላይ አድፍጠው ሊገድሉት ስለ ፈለጉ፣ ፊስጦስ ለእነርሱ እንዲያዳላላቸውና ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው አጥብቀው ለመኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጳውሎስንም ሲቃወም እንዲያደላላቸው እየለመኑ፥ በመንገድ ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ አስበው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው ማለዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጳውሎስንም ሲቃወም እንዲያደላላቸው እየለመኑ፥ በመንገድ ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ አስበው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው ማለዱት። |
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
አለቆቹም ንጉሡን፥ “ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚያች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ፥ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።
ሳውል ግን በእርሱ ላይ ሊያደርጉት የሚሹትን ዐወቀባቸው፤ ሊገድሉትም በቀንና በሌሊት የከተማውን በር ይጠብቁ ነበር።
በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል።
በመንገድ ዘወትር መከራ እቀበል ነበር፤ በወንዝም መከራ ተቀበልሁ፤ ወንበዴዎችም አሠቃዩኝ፤ ዘመዶችም አስጨነቁኝ፤ አሕዛብ መከራ አጸኑብኝ፤ በከተማ መከራ ተቀበልሁ፤ በበረሃም መከራ ተቀበልሁ፤ በባሕርም መከራ ተቀበልሁ፤ ሐሰተኞች መምህራን መከራ አጸኑብኝ።