ሐዋርያት ሥራ 23:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደብዳቤውንም ካነበበ በኋላ ከማን ግዛት እንደ ሆነ ጠየቀው። ከኪልቅያ የመጣ መሆኑንም ባወቀ ጊዜ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገረ ገዥውም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ፣ ጳውሎስን ከየትኛው አውራጃ እንደ መጣ ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑን ባወቀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካነበበውም በኋላ የወዴት አውራጃ እንደሆነ ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ባወቀ ጊዜ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገረ ገዥው ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ ጳውሎስን “ከየትኛው ክፍለ ሀገር ነህ?” ሲል ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑን ባወቀ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካነበበውም በኋላ የወዴት አውራጃ እንደ ሆነ ጠየቀው፤ የኪልቅያ ሰው መሆኑንም ባወቀ ጊዜ፦ |
ጳውሎስም፥ “እኔስ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የተወለድሁባትም ሀገር ጠርሴስ የታወቀች የቂልቅያ ከተማ ናት፤ ለሕዝቡም እንድነግራቸው ትፈቅድልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
የነጻ ወጭዎች ከምትባለው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያ፥ ከቂልቅያና ከእስያ የሆኑ ሰዎችም ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር።