ሐዋርያት ሥራ 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማግሥቱም የሻለቃው አይሁድ የሚከሱት ስለ ምን እንደሆነ ያውቅ ዘንድ ወደደና ከእስራቱ ፈታው፤ ሊቃነ ካህናቱና ሸንጎውም ሁሉ እንዲመጡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም አምጥቶ በፊታቸው አቆመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም የጦር አዛዡ፣ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ስለ ፈለገ ፈታው፤ ከዚያም የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ አባላት በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም አውርዶ በፊታቸው አቆመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግሥቱም አይሁድ የከሰሱት በምን ምክንያት እንደሆነ እርግጡን ያውቅ ዘንድ አስቦ ፈታው፤ የካህናት አለቆችና ሸንጎውም ሁሉ ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ፤ ጳውሎስንም አውርዶ በፊታቸው አቆመው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ አዛዡ፥ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበት ትክክለኛ ምክንያት ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ፈለገ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና የሸንጎው አባሎች በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ ጳውሎስንም ከእስራቱ ፈቶ ወሰደና በፊታቸው አቀረበው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማግሥቱም አይሁድ የከሰሱት በምን ምክንያት እንደ ሆነ እርግጡን ያውቅ ዘንድ አስቦ ፈታው፥ የካህናት አለቆችና ሸንጎውም ሁሉ ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ፥ ጳውሎስንም አውርዶ በፊታቸው አቆመው። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ አንሥቶ እጁንና እግሩን በገዛ እጁ አስሮ እንዲህ አለ፥ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ የዚህን መታጠቂያ ጌታ አይሁድ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያስሩታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።”
እንዲቀጡም ከዚያ ያሉትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ወደ አሉ ወንድሞች እንድሄድ ከእነርሱ ዘንድ የሥልጣን ደብዳቤ የተቀበልኋቸው ሊቀ ካህናቱና መምህራን ሁሉ ይመሰክራሉ።
ጳውሎስም በአደባባዩ ወደአሉት ሰዎች አተኵሮ ተመለከተና፥ “እናንተ ሰዎች ወንድሞች፥ እኔስ እስከዚች ቀን ድረስ በመልካም ሕሊና ሁሉ እግዚአብሔርን ሳገለግል ኑሬአለሁ” አላቸው።
አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።”
ልጁም እንዲህ አለው፥ “አይሁድ አጥብቀህ የምትመረምረው መስለህ ጳውሎስን ነገ ወደ ሸንጎ ታወርድላቸው ዘንድ ሊማልዱህ እንዲህ መክረዋል።
ጳውሎስም እኩሌቶቹ ሰዱቃውያን እኩሌቶቹም ፈሪሳውያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪሳዊ የፈሪሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስፋና ስለ ሙታን መነሣትም ይፈረድብኛል” ብሎ በአደባባይ ጮኸ።
ጳውሎስም፥ “በጥቂትም ቢሆን፥ በብዙም ቢሆን አንተ ብቻ ሳትሆን ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ ከእስራቴ በቀር እንደ እኔ እንዲሆኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ።”
ይህንም በሰሙ ጊዜ ጥዋት ገስግሠው ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ፤ ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ግን ጉባኤውንና ከእስራኤልም ቤት ሽማግሌዎችን ሁሉ ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም ያመጡአቸው ዘንድ ወደ ወኅኒ ቤት ላኩ።