ሐዋርያት ሥራ 23:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ልጁም እንዲህ አለው፥ “አይሁድ አጥብቀህ የምትመረምረው መስለህ ጳውሎስን ነገ ወደ ሸንጎ ታወርድላቸው ዘንድ ሊማልዱህ እንዲህ መክረዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ልጁም እንዲህ አለው፤ “አይሁድ ስለ እርሱ ትክክለኛ የሆነ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የፈለጉ በመምሰል፣ ጳውሎስን ነገ ሸንጎው ፊት እንድታቀርብላቸው ሊለምኑህ ተስማምተዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 እርሱም “አይሁድ ስለ ጳውሎስ ከፊት ይልቅ አጥብቀህ እንደምትመረምር መስለህ፥ ነገ ወደ ሸንጎ ታወርደው ዘንድ ሊለምኑህ ተስማምተዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ልጁም እንዲህ አለ፤ “አይሁድ የጳውሎስን ነገር በጥብቅ የሚመረምሩ መስለው ነገ ወደ ሸንጎው እንድታቀርብላቸው ሊጠይቁህ ተስማምተዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 እርሱም፦ አይሁድ ስለ ጳውሎስ ከፊት ይልቅ አጥብቀህ እንደምትመረምር መስለህ፥ ነገ ወደ ሸንጎ ታወርደው ዘንድ ሊለምኑህ ተስማምተዋል። Ver Capítulo |