ሐዋርያት ሥራ 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ጻድቅህንም ጥፋትን ያይ ዘንድ አትሰጠውምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፤ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ቅዱስህንም በመቃብር በስብሶ እንዲቀር አታደርገውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም። |
አንቺም ቅፍርናሆም፥ እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጃለሽ፤ በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና።
እርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ! የእግዚአብሔር ቅዱሱ!” ብሎ ጮኸ።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
እርሱም፥ “በሙሴ ኦሪት፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ እንዳለው፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ የነገርኋችሁ ነገሬ ይህ ነው” አላቸው።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ያለጊዜአችን ልታጠፋን መጣህን? የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ፥ አንተ ማን እንደሆንህ ዐውቅሃለሁ” አለ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ድንጋዩን አንሡ” አላቸው፤ የሟቹ እኅት ማርታም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አራት ቀን ሆኖታልና ፈጽሞ ሸትቶ ይሆናል” አለችው።
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፥ ሥጋዉም በመቃብር እንደማይቀር፥ ጥፋትንም እንደማያይ አስቀድሞ ዐውቆ ተናገረ።
በቀባኸው በቅዱስ ልጅህ ላይ ሄሮድስና ጰንጤናዊው ጲላጦስ ከወገኖቻቸውና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በእውነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።
ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን እንደ ዐይን ጥቅሻ በአንድ ጊዜ እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋል፤ ሙታንም የማይፈርሱ ሁነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።
“በፊላደልፊያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥ የሚከፍት፥ የሚዘጋም የሌለ፤ የሚዘጋ፥ የሚከፍትም የሌለ፤ ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፦